Loading Bible Translation
First-time download in progress. This may take a few seconds…
Amharic Holy Bible Wordproject Bible
7 verses
1መሠረቶቹ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፤
2ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ፥ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል።
3የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፥ በአንቺ የተከበረ ነገር ይባላል።
4የሚያውቁኝን ረዓ���ንና ባቢሎንን አስባቸዋለሁ፤ እነሆ፥ ፍልስጥኤማውያን ጢሮስም የኢትዮጵያም ሕዝብ፥ እነዚህ በዚያ ተወለዱ።
5ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።
6እግዚአብሔር ለሕዝቡ፥ በውስጥዋም ለተወለዱት አለቆችዋ በመጽሐፍ ይነግራቸዋል።
7በአንቺ የሚኖሩ ሁሉ ደስ እንደሚላቸው ይነግራቸዋል።